ጌታዬ አላህ ነው

ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና።} [አል በቀራ፡ 21]

  • ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ።} [አል ሐሽር፡ 22]
  • ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {የሚመስለው ምንም ነገር የለም እርሱ ሰሚ ተመልካች ነው።} [አሽ ሹራ፡ 11]
  • አላህ የእኔም ጌታየ የሁሉ ነገርም ጌታው ነው፤ የሁሉም ንጉስ (ባለቤት) ፣ የሁሉም ፈጣሪ ፣ የሁሉም ሲሳይ ለጋሽ እና የሁሉ ነገርም አስተናባሪ ነው።
  • አምልኮ (ዒባዳ) በብቸኝነት የሚገባው እርሱ ብቻ ነው፤ ከእርሱም ውጭ ሌላ ጌታ የለም፤ ከእርሱም ውጪ ሌላ እውነተኛ አምላክ የለም።
  • አላህ ለራሱ ያፀደቀውና ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ለአላህ ያፀደቋቸው እጅግ ውብ የሆኑ ስሞች እና ምሉዕ የሆኑ ባህሪያት አሉት። እነዚህም የሙሉነት  (የፍጹምነት) እና የውበት ጫፍ የደረሱ ናቸው። እርሱን የሚመስለው ምንም የለም፤ እርሱ ሰሚ ተመልካችም ነው።

ከአላህ እጅግ ውብ የሆኑ ስሞች መካከል፦ 

  • አር-ረዛቅ (ሲሳይን ሰጪ/ለጋሽ)
  • አር-ረሕማን (እጅግ በጣም አዛኝ)
  • አል-ቀዲር (ሁሉን ቻይ የሆነ)
  • አል-መሊክ (የሁሉም ንጉስ)
  • አስ-ሰሚዕ (ሁሉን ሰሚ)
  • አስ-ሰላም (ከእንከን ሁሉ ነፃ የሆነ ፍፁም፤ የሰላም ባለቤት)
  • አል-በሲር (ሁሉን ተመልካች)
  • አል-ወኪል (አስተዳዳሪው፣ የሁሉም ጉዳይ ባለቤት፤ የፍጡሩ ሁሉ ተወካይ)
  • አል-ኻሊቅ (የሁሉም ፈጣሪ)
  • አል-ለጢፍ ( ውስጥ ዓዋቂ)
  • አልካፊ (ለሁሉም የሚበቃ)
  • አል-ገፉር (መሃሪ)

* አንድ ሙስሊም የአላህን ድንቅ ፍጥረታት እና ነገራቶችንም ለባሮቹ እንዴት እንዳገራቸው ያሰላስላል። ሁሉም ፍጡራን ታዳጊዎቻቸው አድገው ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ የሚያደርጉላቸው እንክብካቤ የዚህ አንዱ መገለጫ ነው። ፈጥሮ ለሚራራላቸው አምላክ ጥራት ተገባው። ከርህሩህነቱ መገለጫዎች መካከል ሙሉ በሙሉ (ሓቁን መወጣት የማይችሉ) ደካማ ከመሆናቸውም ጋር እነርሱን የሚረዳ እና ሁኔታቸውንም የሚያስተካክል መሆኑ ተጠቃሽ ነው።

ጌታዬ አላህ ነው

ለባሮቹ ለልባቸውም ለአካላቸውም የሚያስፈልጋቸውን ሲሳይ በመስጠት ላይ ሙሉ አቅሙም ኃላፊነቱም ያለው።

የእጅግ በጣም ሰፊ፣ ሁሉን ነገር  ያካበበ ታላቅ እዝነት ባለቤት የሆነ።

እጅግ በጣም ሰፊ፣ ሁሉን ነገር ያካበበና የታላቅ እዝነት ባለቤት የሆነ።

በታላቅነት፣ በአሸናፊነት እና በአስተናባሪነት ባህሪያት የሚገለፅ፤ ሁሉንም ነገር በባለቤትነት የሚመራ እና የሚያስተናብር ነው።

ምስጢሩንም ሆነ ይፋ የወጣውን ሁሉ የሚሰማ።

ከማንኛውም ዓይነት ጉድለት፣ እንከንና ነውር ሁሉ የጸዳ ፍጹም የሆነ።

እይታው ትንሽንም ይሁን ደቃቅ እንኳ ሳያስቀር ሁሉንም ነገር የሚመለከት፤ በውስጣቸው የተደበቀን ሁሉ ጠንቅቆ የሚያውቅ ውስጥ ዓዋቂ ሁሉንም ነገር  የማየት ችሎታ ያለው እይታ ባለቤት የሆነ።

የፍጥረታቱ ሲሳይ ባለ ሙሉ ኃላፊነት፣ ጉዳዮቻቸውን በሚበጃቸው መልኩ የሚያስተናብር፤ በእርሱ ለሚያምኑና እርሱን ለሚፈሩ  ወዳጆቹ ጉዳያቸውን የሚያመቻች፣ ለጉዳያቸው በቂያቸው የሆነ።

ቀዳሚ አምሳያ በሌለበት ሁኔታ (ያለ ቅድመ አምሳያ) ነገሮችን ፈጥሮ ህልውና የሰጣቸው።

ባሮቹን የሚያከብር፣ የሚራራላቸው እና ልመናቸውንም ተቀብሎ ምላሽ የሚሰጣቸው።

ያ ባሮቹ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ በቂያቸው የሆነ፤ በእርዳታውም ከእርሱ ውጪ ካሉት ሁሉ የሚብቃቁበት ወይም የእርሱ እርዳታ ከሌሎች የሚያብቃቃ።

ባሮቹን ከኃጢኣታቸው መዘዝ እና ቅጣት የሚጠብቃቸው።

የእኔ ነብይ ሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ናቸው

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
{ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፤ በምእምናን (ላይ) ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ።} [አትተውባ፡128]

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም።} [አል-አንቢያእ: 107] 

ሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) የእዝነቱ ነብይ

ስማቸው ሙሐመድ ኢብን ዐብደላህ ይባላሉ፤ የነብያትም የመልእክተኞችም መደምደሚያ ናቸው። አላህ የእስልምናን ሃይማኖት ያስተምሩ ዘንድ ወደ ሰው ልጆች ሁሉ ላካቸው፤ ሰዎችን ወደ መልካም ነገር ያመላክቱ ዘንድ በተለይም ታላቅ የሆነውን የአላህ ብቸኛ ተመላኪነት ተውሒድ እንዲያስተምሩ እንዲሁም ከመጥፎ ነገሮች ሁሉ እንዲከለክሏቸው በተለይም ከባድ ከሆነው ወንጀል ሺርክ እንዲያስጠነቅቁ ነው የላካቸው።

እርሳቸውም ይሁን ከእርሳቸው በፊት የነበሩት ነብያት ሁሉ ተልዕኳቸው የነበረው አላህን ያለ ምንም ተጋሪ በብቸኝነት ወደ ማምለክ ጥሪ ማድረግ ነው። 

ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን ባህሪያት መካከል፡- 

  • እውነተኝነት
  • ርህራሄ
  • ቻይነት
  • ታጋሽነት
  • ጀግንነት
  • ቸርነት
  • መልካም ስነምግባር
  • ፍትሃዊነት
  • ትህትናይቅር ባይነት (ከብዙ በጥቂቱ ናቸው)።

 

የተከበረው ቁርኣን የጌታዬ አላህ ቃል

የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
{እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ በእርግጥ አስረጅ መጣላችሁ፤ ወደእናንተም ገላጭ የሆነን ብርሃን (ቁርኣንን) አወረድን።} [አን-ኒሳእ: 174]

የተከበረው ቁርአን ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ሰዎችን ከጨለማ ወደ ብርሃን ሊያወጡበትና ወደ ቀጥተኛው መንገድም ሊመሩበት ዘንድ የወረደላቸው የአላህ ቃል ነው።
ያነበበው ሰው ታላቅ ምንዳ ያገኝበታል፤ ትዕዛዛቱን የፈፀመ ደግሞ ቅኑን መንገድ ይከተላል።

የእስልምና ምሰሶዎች (ማዕዘናት) መማሪያ

የአላህ መልዕክተኛ ሰላትና ሰላም በእርሳቸዉ ላይ ይሁን እንዲህ ብለዋል፦
(እስልምና በአምስት (ማዕዘናት) ላይ ተገንብቷል፦ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣ ሶላትን ደንቡንና ሥርዓቱን ጠብቆ መስገድ፣ ዘካ መስጠት፣ የረመዳንን ወር መጾም እና ሐጅ ማድረግ (የአላህን ቤት መጎብኘት)) ናቸው።

የእስልምና ማዕዘናት ማንኛውም ሙስሊም ሊፈፅማቸው የሚገቡ የአምልኮ ተግባራት ናቸው። የእነዚህ ማዕዘናት ግዴታነት ካላመነ እና እና ሁሉንም ካልተቀበለ በስተቀር የአንድ ሰው እስልምና ተቀባይነት አይኖረውም። ምክንያቱም እስልምና የታነፀው በእነርሱ ነውና፤ ለዚህም ነው የእስልምና ምሰሶዎች (ማዕዘናት) ተብለው የተሰየሙት።

እነዚህም ማዕዘናት የሚከተሉት ናቸው፦

 

የእስልምና ምሰሶዎች (ማዕዘናት) መማሪያ

የመጀመሪያው ማዕዘን

ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር።

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {እነሆ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እወቅ።} [ሙሐመድ፡ 19]

አላህ እንዲህም ብሏል፡- {ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን (ላይ) ርኅሩኅ አዛኝ የሆነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ።} [አትተውባ፡128]

  • ላኢላሃ ኢለሏህ ማለት፦ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ማለት ነው።
  • ሙሐመደን ረሱለሏህ ማለት ደግሞ፦ ያዘዙትን መታዘዝ ፣ የተናገሩትን እውነት ብሎ መቀበል ፣ የከለከሉትን እና ያስጠነቀቁቱን ነገር መራቅ እንዲሁም አላህን እርሳቸው በደነገጉት (ባስተማሩት) መልኩ ማምለክን የሚያስፈርድ ነው።

 

ሁለተኛው ማዕዘን

ሰላትን በአግባቡ መስገድ።

የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡- {ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ።}  [አል በቀራ፡ 110] 

  • ሶላትን መስገድ ማለት፦ ሶላትን አላህ በደነገገው እና መልእክተኛው ሙሐመድ (የአላህ ሰላት እና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ባስተማሩት መንገድ መስገድ ነው።

 

ሦስተኛ ማዕዘን

ዘካ መስጠት።

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {ዘካንም ስጡ።} [አል በቀራ፡ 110]

  • ከፍ ያለው አምላክ አላህ ዘካን የአንድ ሙስሊምን እምነት እውነተኝነት መፈተኛ እንዲሆን፣ አላህ  ለዋለለት የገንዘብ ፀጋ ማመስገኛ  እንዲሆን እና ለድሆችና ለችግረኞችም ድጋፍ ሊሆን ዘንድ ግዴታ አድርጎታል። የዘካ ግዴታን መወጣት የሚቻለው ለሚገባቸው በመስጠት ነው።
  • ይህም የተወሰነ መጠን ላይ ከደረሰ ገንዘብ ውስጥ የሚወጣ የተወሰነ የግዴታ መጠን ነው፤ አላህ በተከበረው ቁርኣን ውስጥ ለጠቀሳቸው ስምንት ዓይነት ምድቦች የሚሰጥ ነው፤ ከነዚህም መካከል ድሆች እና ችግረኞች ይገኙበታል።
  • በአፈፃፀሙ ሂደት ላይ እዝነት እና ደግነትን መላበስ፣ የሙስሊሙን ስነ-ምግባር እና ሀብት ማጥራት፣ የድሆችን እና የችግረኞችን ነፍስ ማርካት፣ በህዝበ ሙስሊሙ መካከል ያለውን የፍቅር እና የወንድማማችነት ትስስር ማጠናከርን ይዟል። በዚህም ምክንያት መልካም የሆነ ሙስሊም ለሌሎች ሰዎች የሚሰጠውን ደስታ በማሰብ ዘካን እርካታ እየተሰማውና በማውጣቱ ደስተኛ እየሆነ ነው የሚሰጠው።
  • የዘካው መጠን ከወርቅ፣ ከብር፣ ከገንዘብ ኖቶችና ለትርፍ ከተዘጋጁ ለግዥና ሽያጭ የተቀመጡ የንግድ ዕቃዎች ገንዘብ ውስጥ 2.5% ነው። (ዘካ የሚወጣውም ንብረቱ) ለዘካ የተወሰነለት መጠን ላይ ደርሶ (በጨረቃ አቆጣጠር) አንድ ዓመት ከሞላው ነው።
  • አብዛኛውን የዓመቱን ጊዜ ባለቤቱ ሳይመግባቸው (የቀለ ወጪ ሳያወጣባቸው) ከመሬቱ ሳር የሚግጡ የሆኑ ለዘካ በተወሰነው መጠን ብዛት የደረሱ እንስሳት (ግመል፣ ላም እና በግ) ያለው ሰው ዘካ ማውጣት ግዴታ እንደሚሆንበት ሁሉ ማለት ነው።
  • የተወሰነ መጠን ላይ የደረሰ ከምድር የሚገኝ እህል እና ፍራፍሬ እንዲሁም ማዕድን እና ከምድር ውስጥ ተቀብሮ ከተጋኘ ድልብ ላይም ዘካህ ግዴታ ነው።

 

አራተኛ ማዕዘን

የረመዳንን ወር መፆም።

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና።} [አል በቀራ፡ 110]

  • ረመዳን፡- በሂጅሪያ የዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ዘጠነኛው ወር ሲሆን ሙስሊሞች ዘንድ የተከበረና የተቀደሰ ወር ነው፤ ከቀሪዎቹ የዓመቱ ወራት የተለየ ደረጃ ያለው ወር ነው፤ ሙሉውን ወር መፆም ከአምስቱ የኢስላም መሰረቶች (ማዕዘናት) መካከል አንዱ ነው።
  • የረመዳን ጾም ማለት፡- የተባረከውን የረመዳን ወር በቆየባቸው ቀናት ውስጥ ጎህ ከቀደደበት ጊዜ ጀምሮ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከግብረ ስጋ ግንኙነት እና ሌሎች ፆምን ከሚያበላሹ ነገሮች በመከልከል ሙሉ ቀኑን ከፍ ያለውን አምላክ አላህ ማምለክ ነው።

 

አምስተኛው ማዕዘን

ሐጅ ማድረግ የተከበረውን አላህን ቤት መጎብኘት።

የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡- {ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መሄድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው።} [አሊ-ዒምራን፡ 97]

  • ሐጅ ማድረግ ወጪውን ለቻለ ሰው በሕይወቱ አንድ ጊዜ ብቻ ግዴታ ነው። ይሀውም ወደ ተከበረው ቤት እና መካ አል-ሙከረማህ ወደሚገኙ ቅዱሳን ስፍራዎች በመሄድ የተወሰኑ የአምልኮ ተግባራትን በተወሰነ ጊዜ መፈፀም ነው። ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እና ከእርሳቸውም በፊት የነበሩ ነብያትም ሐጅ አድርገዋል። እንዲሁም አላህ ኢብራሂምን ሰዎችን ወደ ሐጅ ጉዞ እንዲያደርጉ እንዲያውጁ አዟቸዋል። ይህንንም አላህ በተከበረው ቃሉ  በቁርኣን ነግሮናል፦ {(አልነውም)፡- በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና።} [አል-ሐጅ: 27]

 

የኢማን ምሰሶዎች (ማዕዘናት) መማሪያ

የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለ ኢማን (እምነት) ተጠይቀው እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፦ “በአላህ፣ በመላዕክቱ፣ በመጻሕፍቱ፣ በመልክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በቀደር መልካምም ሆነ መጥፎ በሆነ (የአላህ ቅድመ ውሳኔ) ማመን ነው”
የእምነት ማዕዘናት በልብ ከሚፈፀሙ የአምልኮ ተግባራት የሚመደቡ ሲሆኑ፤ በእነርሱ ማመን በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፤ በእነርሱ እስካላመነ ድረስ የአንድ ሰው እስልምና ትክክለኛ አይሆንም፤ ለዚህም ነው የእምነት ማዕዘናት ተብለው የተሰየሙት። በኢማን ማዕዘናት እና በኢስላም ማዕዘናት መካከል ያለው ልዩነት፦ የኢስላም ማዕዘናት አንድ ሰው በአካሉ የሚፈጽማቸው በግልፅ የሚታዩ ተግባራት ሲሆኑ ለምሳሌ ሁለቱን የምስክርነት ቃላት በአንደበት መመስከር፣ ሶላት እና ዘካን መጥቀስ ይቻላል። የኢማን ማዕዘናት ደግሞ በልብ የሚፈፀሙ ተግባራት ሲሆኑ አንድ ሰው በልቡ የሚሠራቸው ናቸው። ለምሳሌ በአላህ፣ በመጽሐፍቱ እና በመልዕክተኞቹ ማመንን መጥቀስ ይቻላል።

የኢማን (እምነት) ፅንሰ-ሀሳብ እና ትርጉሙ፡-
ኢማን ማለት በአላህ፣ በመላዕክቱ፣ በመጻሕፍቱ፣ በመልዕክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀን እና መልካምም ይሁን መጥፎ በቀደር በቁርጠኝነት በልብ ማመን፤ መልእክተኛው ይዘው የመጡትን (አስተምህሮ) ሁሉ መከተል እና ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም የላኢላሃ ኢለላህ (ከአላህ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ አምላክ አለመኖሩን) በምላስ መመስከር ፣ ቁርኣን ማንበብ፣ ሱብሐነላህ (ጥራት ለአላህ ተገባው) ላኢላሃ ኢለላህ ማለት እና አላህን ማወደስ መሰል ቃላቶችን በአንደበት መናገርን ሁሉ የሚያካትት ነው።
በጉልህ አካል ከሚሠሩት መካከል፡- እንደ ሶላት፣ ሐጅ፣ ጾም... የሚጠቀሱ ሲሆን በውስጣዊ አካል ከሚሰሩት መካከል ደግሞ አላህን መውደድና መፍራት፣ በእርሱ መመካትና ለእርሱ መታመን (ኢኽላስ) መሰል የልቦና ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው።
የዘርፉ ሊቃውንቶች (ዑለማዎች) ኢማንን ባጭሩ ሲገልፁት፡- በልብ የሚታመን፣ በምላስ (በአንደበት) የሚነገር፣ በአካል ክፍሎች የሚተገበር አላህን በመታዘዝ የሚጨምር እና አላህን በማመፅ (ባለመታዘዝ) ደግሞ የሚቀንስ ነው ይላሉ።

የኢማን ምሰሶዎች (ማዕዘናት) መማሪያ

የመጀመሪያው ማዕዘን

በአላህ ማመን

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {ምእመናን ማለት እነዚያ በአላህና በመልክተኛው ያመኑት ናቸው።} [አንኑር፡ 62]

  • በአላህ ማመን በጌትነቱ፣ በአምላክነቱ፣ በስምና ባህሪያቱ አላህን ብቸኛ ማድረግን ያጠቃልላል። እንዲሁም የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦

  •  አላህ መኖሩን ማመን።

  •  የበላይና ጥራት የተገባው በሆነው አላህ ጌትነት ማመን፤ እርሱ የነገሩ ሁሉ ባለቤት፣ ፈጣሪ፣ ሲሳይ ሰጪና አስተናባሪ መሆኑን ማመን።

  •  በአምላክነቱ ማመን፤ አላህ በብቸኝነት ሊመለክ የሚገባው መሆኑን ፤ የአምልኮ ተግባራትን ያለ አንዳች ተጋሪ ለእርሱ ብቻ ማድረግ፤ ከእነርሱም መካከል ሶላት፣ ዱዓ ( ተማፅኖ)፣ ስለት፣ እርድ፣ እርዳታን መፈለግ፣ ጥበቃን መፈለግ እና ሌሎችን ዒባዳዎች ሁሉ (ለአላህ ብቻ ማድረግ)።

  •  አላህ ለራሱ ያረጋገጣቸውን ወይም ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ያፀደቁለት በሆኑት ውብ ስሞችና ምሉዕ በሆኑት ባህርያቱ ማመን፤ አላህ እርሱን ከመግለፅ ያወገዛቸውንና ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም እርሱን ከመግለፅ ያወገዟቸውን ስምና ባሕርያት ውድቅ ማድረግ፤ የአላህ ስምና ባህሪያት በሙሉነት (ፍፁምነት) እና በውበት ጥግ የደረሱ ናቸው። (እርሱንም የሚመስለው ምንም ነገር የለም፤ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው)።

 

ሁለተኛው ማዕዘን

በመላኢኮች ማመን

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {ምስጋና ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ባለ ሶስት ሶስትም፣ ባለ አራት አራትም ክንፎች የኾኑ መልክተኞች አድራጊ ለኾነው አላህ ይገባው፡፡ በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።} [ፋጢር፡ 1]

  • መላእክት የማይታዩ ዓለም፤ ከብርሃን የተፈጠሩ እንዲሁም ለእርሱ ታዛዥና ተገዢ ያደረጋቸው የአሏህ ባርያዎቹ መሆናቸውን እናምናለን።
  • ታላቅ የሆኑ ፍጥረት ናቸው፤ ስለ ብቃታቸውም ይሁን ስለቁጥራቸው የሚያውቀው የበላይ የሆነው አላህ ብቻ ነው። እያንዳንዳቸውም አላህ ለነርሱ ለይቶ የሰጣቸው መገለጫዎች፣ ስሞች እና ኃላፊነቶች አሏቸው፤ ከእነርሱም መካከል ጂብሪል ከአላህ ወደ መልዕክተኞች ወሕይ (ራዕይ) እንዲያወርድ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

 

ሦስተኛው ማዕዘን

በመጽሐፍቱ ማመን

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርኣን) ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ (ለአላህ) ታዛዦች ነን} በሉ፡፡ [አል-በቀራህ: 136]

  • መለኮታዊ (ቅዱሳን) መጻሕፍት ሁሉ የአላህ ቃል መሆናቸው ጽኑ (ቁርጠኛ) እምነት ማሳደርና እውነት ብሎ መቀበል።
  • ከአላህ ዘንድ በመልእክተኞቹ ላይ የተወረደ ወደ ባሮቹ (የተላለፈ) ግልፅ የሆነ እውነት ነው።
  • አላህ መልዕክተኛውን ሙሐመድን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን ወደ ሰዎች ሁሉ በመላክ (ከእርሳቸው በፊት ለነበሩ ነብያት የተሰጡ) ቀደምት ህግጋትን ሁሉ ለእርሳቸው በሰጣቸው ህግ እንዲሻሩ አድርጓል፤ እና የተከበረውን ቁርኣንንም የሁሉም ሰማያዊ (መለኮታዊ) መጽሃፍት የበላይ (ተቆጣጣሪ) እና ሻሪ እንዲሆን አድርጎታል። እንዲሁም አላህ የተከበረውን ቁርኣን ከማንኛውም ዓይነት ለውጥ ወይም መዛባት ለመጠበቅ ሙሉ ኃላፊነቱንም ወስዷል፡- {እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን} [አል-ሒጅር: 9]. ምክንያቱም ቅዱስ ቁርኣን አላህ ለሰው ልጆች ያወረደው የመጨረሻው የእርሱ መጽሐፍ ነው፤ መልዕክተኛውም ሙሐመድ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን የመጨረሻ መልዕክተኛ ናቸው፤ የእስልምና ሃይማኖትም አላህ እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ለሰው ልጆች የወደደላቸውና የመረጠላቸው ሃይማኖት ነው፡- {አላህ ዘንድ የተወደደው ሀይማኖት እስልምና ነው} [አሊ-ዒምራን ፡19]።

የበላይ የሆነው አላህ በመጽሐፉ (ቁርኣን) ውስጥ የጠቀሳቸው መለኮታዊ መጻሕፍት የሚከተሉት ናቸው፡-

  • 1 የተከበረው ቁርኣን፡- አላህ በነብዩ ሙሐመድ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን ላይ ያወረደው።
  • 2 ተውራት (ኦሪት)፡- አላህ በነቢዩ ሙሳ (ሙሴ) የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን ላይ ያወረደው።
  • 3 ኢንጂል (ወንጌል)፦ አላህ በነቢዩ ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን ላይ ያወረደው።
  • 4 ዘቡር (መዝሙረ ዳዊት)፦ አላህ በነቢዩ ዳዉድ (ዳዊት) የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን ላይ ያወረደው።
  • 5 ሱሑፍ ኢብራሂም፦ አላህ በነቢዩ ኢብራሂም (አብረሃም) የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን ላይ ያወረደው።

አራተኛው ማዕዘን

በመልዕክተኞች ማመን

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል።} [አን-ነሕል፡ 36]

  • ኃያሉ አላህ በሁሉም ህዝቦች ውስጥ መልዕክተኞችን ብቸኛና ምንም ዓይነት አጋር የሌለውን አላህ በብቸኝነት እንዲገዙት እና ከእርሱም ውጪ በሚመለኩት ሁሉ እንዲክዱ ጥሪ እንዲያደርጉ እንደላካቸው ጽኑ (ቁርጠኛ) እምነት ማኖር ነው።
  • ሁሉም ነብያት ሰዎች፣ ወንዶች፣ የአላህ ባሮች፣ እውነተኞችና የታመኑ፣ አላህን ፈሪና ታማኝ፣ ወደ ቅን ጎዳና የተመሩና ሌሎችንም የሚመሩ፣ እውነተኝነታቸውን ማረጋገጥ የሚችሉ ተአምራትን አላህ የሰጣቸው እና አላህ የሰጣቸውን መልዕክት ሁሉ ያስተላለፉ ናቸው፤ ሁሉም ነብያት በግልፅ እውነት እና በትክክለኛ መመሪያ ላይ ነበሩ።
  • ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተላኩት ነብያት የዲን መሰረት (ሃይማኖታዊ መርህ) የሆነው ጥሪያቸው አንድ አይነት ነው፤ ይሀውም አላህን በአምልኮ ብቸኛ ማድረግና በእርሱ ላይ ከማጋራት መቆጠብ ነው።

 

%MCEPASTEBIN%

አምስተኛው ማዕዘን

በመጨረሻው ቀን ማመን

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {አላህ ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም፡፡ ወደ ትንሣኤ ቀን በርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል፡፡ በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው?።} [አንኒሳእ፡ 87]

  • ልዕለ ኃያል የሆነው ጌታችን በተከበረው መጽሐፉ (ቁርኣን) ወይም ነቢያችን ሙሐመድ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን የነገሩንን የሰው ልጅ መሞት፣ ከሞተም በኋላ መቀስቀስ፣ ትንሣኤ፣ ምልጃ፣ ሚዛን፣ ምርመራ (ሒሳብ መደረግ)፣ ጀነት እና ጀሀነም እና ሌሎች ከመጨረሻው ቀን ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ሁሉ በጽኑ ማመን ነው።

 

ስድስተኛው ማዕዘን

መልካምም ሆነ መጥፎ በአላህ ቀደር (ቅድመ ውሳኔ) ማመን

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው።} [አል ቀመር፡ 49]

  • በዚህ ዓለም ውስጥ በፍጥረታት ላይ የሚደርሰው ክስተት ሁሉ ጥራት ይገባውና የልዑሉ አላህ ዕውቀት እና ቀደር (ቅድመ ውሳኔ) መሆኑን፤ እነዚህ ቅድመ ውሳኔዎች የተጻፉትም የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት መሆኑን፤ የሰው ልጅ ነፃ ምርጫ እንዳለውና የድርጊቱ እውነተኛ ፈፃሚ ራሱ መሆኑንም እናምናለን። ይህ ሁሉ ታዲያ ከአላህ እውቀትና ፈቃድ ውጭ የሚሆን አይደለም።

በቀደር (ቅድመ ውሳኔ) ማመን አራት ደረጃዎች ላይ የተመሠረተ ነው ፦

  • አንደኛሁሉን የሚያካትትና ሙሉ በሆነው የአላህ ዕውቀት ማመን።
  • ሁለተኛእስከ ዕለተ ትንሳኤ ድረስ የሚሆነውን (የሚከሰተውን) ነገር ሁሉ አላህ እንደጻፈው ማመን።
  • ሦስተኛተፈፃሚ በሆነው የአላህ ፈቃድ እና ሙሉ በሆነው ኃይሉ ማመን፤ አላህ የሚፈልገው ይሆናል የማይፈልገው ነገር ደግሞ አይሆንም።
  • አራተኛአላህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው ብሎ ማመንና በመፍጠሩ ላይም ምንም ዓይነት አጋር እንደሌለው ማመን።

የዉዱእ አደራግን እማራለሁ

የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡- {አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል።} [አል በቀራህ፡ 222]

የአላህ መልዕክተኛ ሰላትና ሰላም በእርሳቸዉ ላይ ይሁን እንዲህ ብለዋል፦ “እንዲሁ እኔ እንዳደረግኩት ውዱእ አድርጎ ከዚያም ምንም ሳይወሰወስ ሁለት ረከዓ የሰገደ ያለፈ ወንጀሉን አሏህ ይምርለታል”

የሶላትን ትልቅ ደረጃ ከሚያሳዩ ነገሮች መካከል አንዱ አላህ ከሶላት በፊት ጦሀራን (መፀዳዳት) መደንገጉ ነው፤ ለሶላቱ ትክክለኝነትና ተቀባይነትም መስፈርት አድርጎታል፤ ጦሃራ የሶላት ቁልፍ (ለመፈፀም የመጀመሪያው እርምጃ ) ነው፤ ከጥቅሙም መካከል ንቃተ ህሊናን በመጨመር ልብ ሶላት ለመስገድ እንዲናፍቅ ያደርጋል።
የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን እንዲህ ብለዋል፦ “ንፅህና የእምነት ግማሽ ነው ... ሶላት ደግሞ ብርሃን ነው”።
የአላህ መልዕክተኛ ሰላትና ሰላም በእርሳቸዉ ላይ ይሁን እንዲህ ብለዋል፦ “ ዉዱእን አሳምሮ በአግባቡ ያደረገ፤ ኃጢአቱ ከአካሉ ይወጣል (ይራገፍለታል)።”
አንድ የአላህ ባሪያ በዉዱእ አካላዊ ንጽህናውን የሚጠብቅ ሲሆን፤ ይህን የአምልኮ ተግባር በኢኽላስ (ሥራውን ለአላህ ብቻ ጥርት በማድረግ) እና የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን መመሪያ በመከተል ውስጣዊ ንፅህናውን ይጠብቃል።

ውዱእ ማድረግ ግዴታ የሚያስፈልጋቸው የአምልኮ ተግባራት፦

  • 1 ግዴታም ሆነ ግዴታ ያልሆኑ (ሱና) ሶላት
  • 2 በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ለማድረግ
  • 3 ሙስሐፍ (ቁርአን) መንካት
  • ዉዱእም ሆነ የገላ ትጥበትን የማከናውነው ጣሃራ (ንፁህ) በሆነ ውኃ ነው።
  • ንፁህ ውኃ የሚባለው፦ ከሰማይ የወረደ ወይም ከምድር የፈለቀ ውኃ ሁሉ ሲሆን ተፈጥሯዊ ይዘቱን ሳይቀይር የቆየ ከሆነና የውሃ ንፅህናን ከሚያሳጡ ሦስቱ ባህሪያት የቀለም፣ የጣዕም ወይም የሽታ መለወጥ ያላጋጠመው ከሆነ ነው።

የዉዱእ አደራግን እማራለሁ

ኒያህ ማድረግ (በልብ ማሰብ) ፤
ኒያህ ማለት ወደ አላህ መቃረቢያ አምልኮን ለመፈፀም በልብ ውስጥ ያለን ቁርጠኝነት ነው።

በሁለተኛ ደረጃ፡ ሁለት መዳፎችን መታጠብ

መጉመጥመጥ (መድመዳህ)
መድመዷህ ማለት፦ ውኃ አፍ ውስጥ አስገብቶ ተጉመጥምጦ መትፋት ነው።

መሰርነቅ (ኢስቲንሻቅ)
መሰርነቅ ማለት፦ ወደ ውስጥ አፍንጫ ውኃን በደንብ መሳብ ነው።
ኢስቲንሣር ማለት፦ በአፍንጫ ውስጥ ያሉ እንደ ንፍጥ እና መሰል ነገራቶችን ማስወጣት ነው።

ፊትን ማጠብ

የፊት ድንበሩ፡-

ፊት ማለት: የሚቅጣጩበት የሰውነት ክፍል ነው።

የጎን ስፋቱ: ከአንዱ ጆሮ እስከ ሌላኛው ጆሮ ድረስ ሲሆን።

የፊት ወሰን ርዝመቱ ደግሞ፡ በተለምዶ ፀጉር ከሚጀምርበት የግንባር ክፍል እስከ የአገጫችን መጨረሻ ድረስ ነው።
ፊቱን ማጠብ በላዩ ላይ ያሉትን ነገሮች ማለትም እንደ ለስላሳ ፀጉር እንዲሁም “አል-በያድ” እና “አል-ዒዛር” ማጠብን ያጠቃልላል።

አልበያድ ማለት፦ በጆሮው ፊት ለፊት ላይ የበቀለ ፀጉር ነው።

አልዒዛር ማለት ደግሞ፦ በጆሮው ትይዩ ሆኖ ከራስ ፀጉር ወደ አገጭ የሚወርደው ፂም (ሪዝ) ነው።

ሌላኛው ፊትን ከማጠብ የሚካተተው ሁሉንም ጎልተው የሚታዩትን የፂም ፀጉር እና ከእርሱ ዘልቆ ከውስጥ ያለውንም ማጠብ ነው።

ከጣት ጫፎች ጀምሮ እስከ ክርኖች ድረስ እጆችን መታጠብ
ክርኖችን ማጠብ እጆችን ከመተጠብ ግዴታ ውስጥ ይካተታል።

በተነከሩ እጆች ጭንቅላትን እና ጆሮን አንድ ጊዜ ማበስ
ይሀውም ከፀጉር መብቀያው ግንባር ይጀምርና ወደ ጭንቅላቱ ጀርባ ማጅራቱ ድረስ ይወስዳቸውና ከዚያም እንደገና ወደ ጀመረበት በመመለስ ነው።
ጠቋሚ ጣቶቹን ወደ ጆሮው ያስገባል።
አውራ ጣቱን ከጆሮው ጀርባ በማሳለፍ (በማሻገር) የጆሮውን ፊት እና ኋላ ያብሳል።

እግሮቹን ከእግር ጣቶች መጀመሪያ አንስቶ እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ ማጠብ፤ ቁርጭምጭሚቶቹን ማጠብ ግዴታ መታጠብ ካለበት የእግሮቹ ክፍሎች ውስጥ ይካተታል።
ቁርጭምጭሚቶች የሚባሉት፡- በእግር ባት ስር ወጣ ብለው የሚታዩት አጥንቶች ናቸው።

ዉዱእን የሚያበላሹ ነገሮች

  • 1 እንደ ውኃ ሽንት፣ ሰገራ፣ ፈስ፣ መንይ እና መዝይ መሰል በውኃ ሽንት እና አይነ ምድር መውጫ ቦታዎች በኩል የሚወጡ ነገሮች፡፡
  • 2 ጭልጥ ባለ እንቅልፍ ወይም ራስን በመሳት ወይም በስካር ወይም በእብደት ምክንያት የአዕምሮ መሸፈን
  • 3 የገላ ትጥበትን ግዴታ የሚያደርጉ ነገሮች ሁሉ፤ ለምሳሌ ጀናባ መሆን፣ የወር አበባ እና የወሊድ ደም መፍሰስ።

አንድ ሰው (ከሽንት ወይም ከሰገራ) ተፀዳድቶ ከጨረሰ በኃላ ቢቻል ንፁህ በሆነ ውኃ - ይህ በላጩ ነው - ካልቻለ ደግሞ ከውኃ ውጪ ባሉ ነጃሳውን ማፅዳት የሚችሉ ንፁህ ሌሎች ነገሮች ለምሳሌ ድንጋይ፣ ወረቀት (ሶፍት) በመሳሰሉት ነጃሳውን ማስወገድ ግዴታ ነው። (በውኋ ምትክ የምንጠቀማቸው ነገሮች) ንፁህና በሚፈቀድ ነገር የተሰሩ ከመሆነቸውም ባሻገር ብዛታቸውም ሶስት ጊዜ ማጽዳት የሚያስችሉ ወይም ከዚያ በላይ መሆን ይገባቸዋል።

በኹፍ እና ካልሲዎች ላይ ማበስ

ኹፍ ወይም ካልሲዎችን በሚለብሱበት ጊዜ በሚከተሉት  ቅድመ ሁኔታዎች  መሰረት እግሮችን መታጠብ ሳያስፈልግ በእነሱ ላይ ማበስ ይቻላል። ቅድመ ሁኔታዎቹም የሚከተሉት ናቸው፦

  • 1 ኹፎቹ የተለበሱት/የተደረጉት ከትንሹ ሐደሥም ይሁን ከትልቁ ሐደሥ ሙሉ በሙሉ ጠሀራ ከሆነ በኋላ መሆን አለበት።
  • 2 ካልሲዎቹ ወይም ኹፎቹ ጡሀራ መሆን አለባቸው፤ ነጃሳ መሆን የለባቸውም።
  • 3 የታበሱት (ለማበስ) በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ውስጥ መሆን አለበት።
  • 4 በህጋዊ (ሐላል) በሆነ መልኩ የተገኙ መሆን አለባቸው፤ ለምሳሌ የተሰረቁ ወይም የተዘረፉ መሆን የለባቸውም።
  • “ኹፍ” የሚባሉት፦ ከቀጭን ቆዳ የተሠሩ የእግር ጫማዎችና የመሳሰሉት ናቸው፤ ተረከዝን የሚሸፍኑ እስከሆኑ ድረስ ጫማዎችም ብይናቸው ተመሳሳይ ነው።

  • ካልሲ የሚባለው፡- አንድ ሰው በእግሩ ላይ የሚለብሰው ከጥጥና ከመሳሰሉት የሚሠራ ነው፤ የእግር ሹራብ በመባልም ይታወቃል።

በኹፍ እና ካልሲዎች ላይ ማበስ

በኹፍ ላይ ማበስ የመደንገግ ጥበቡ፦
በኹፍ ላይ ማበስ የተፈቀደበት ጥበብ ኹፋቸውን ወይም ካልሲያቸውን አውልቀው እግራቸውን ለማጠብ ለሚከብዳቸው ሙስሊሞች በተለይም በክረምት እና በከባድ ብርድ እንዲሁም በሚጓዙበት ወቅት ለማግራት እና ቀለል ለማድረግ ነው።

የማበሻ ጊዜ ገደብ:-

ለነዋሪ፦ አንድ ቀን ከነሌሊቱ (24 ሰዓት)።

ለመንገደኛ፦ ሦስት ቀናት ከነለሊታቸው (72 ሰዓት) ።

የማበሻ ጊዜ ስሌት የሚጀምረው  ውዱእ ካጠፋ በኋላ በኹፍ ወይም በካልሲ ላይ ካበሰበት ጊዜ ጀምሮ ነው።

በኹፍ ወይም ካልሲ ላይ የሚታበስበት ስርዓት፦   

  • 1 እጆችዎን እርጥብ ያድርጉ። 
  • 2 ያረጠቡትን እጅዎን በእግሮ ላይኛው ክፍል ላይ (ከጣቶቾ ጫፍ እስከ እግሮ ጫፍ ድረስ) ያሳልፉ።
  • 3 የቀኝ እግር በቀኝ እጅ፤ የግራ እግርን በግራ እጅዎ ያብሱ።

ማበስን የሚያበላሹ ነገሮች፦

  • 1 የገላ ትጥበትን  ግዴታ የሚያደርጉ ነገሮች ሁሉ።
  • 2 የማበሻ ጊዜ ገደብ መጠናቀቅ።

ተየሙም (በአፈር መጽዳዳት)

አንድ ሙስሊም ራሱን የሚያጠራበት ውኃ ማግኘት ካልቻለ ወይም በህመም እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ውኃ መጠቀም ካልቻለና የሶላት ጊዜ እንዳያመልጠዉ ስጋት ካደረበት በአፈር ተያሙም ያደርጋል።

ተየሙም (በአፈር መጽዳዳት)

ይህም በሁለት እጆቹ አፈርን አንድ ጊዜ መታ ያደርጋል፤ በዚያውም ፊቱንና ሁለት መዳፎቹን ብቻ ያብሳል። ተየሙም የሚደረግበት አፈር ጡሀራ መሆኑ ቅድመ መስፈርት ነው።

ተየሙም በእነዚህ ነገሮች ይበላሻል፡-

  • 1 ዉዱእ  የሚያበላሽ ነገር ሁሉ ተየሙምንም ያበላሻል።
  • 2 ተየሙም ያደረገለትን ዒባዳ ከማከናወኑ በፊት ውሀ ማግኘት ወይም በውሀ መጠቀም ከቻለ ተየሙሙ ይበላሻል።

ራሴን ለሶላት አዘጋጃለሁ

ራሴን ለሶላት አዘጋጃለሁ

  • የሶላት ወቅት ሲገባ አንድ ሙስሊም ከትንሹ ሐደሥም ሆነ ተከስቶ ከሆነ ከትልቁ ሐደሥም ራሱን ያጸዳል።

ትልቁ ሐደሥ ማለት፦ መላ ሰውነትን መታጠብ የሚያስፈርድ ነው (ለምሳሌ ግብረስጋ ግንኙነት መፈፀም)።
ትንሽ ሐደሥ ማለት ደግሞ፦ ዉዱእ ማድረግን የሚያስፈርድ ነው።

  • አንድ ሙስሊም ሶላቱን መስገድ የሚገባው ከነጃሳ በጠራ ንፁህ ልብስ እና ንፁህ ሥፍራ እንዲሁም ሀፍረተ ገላውንም (ሶላት ውስጥ መሸፈን ያለበትን የአካል ክፍል) በአግባቡ ሸፍኖ ነው።
  • አንድ ሙስሊም በሶላት ጊዜ ገላውን በአግባቡ  መሸፈንና ተገቢ በሆነ ልብስ  ማጌጥም አለበት። አንድ ወንድ በሶላት ወቅት በእምብርት እና ጉልበቱ መካከል ያለውን የአካሉ ክፍል ሳይሸፍን መስገድ አይፈቀድለትም።
  • ሴት ከሆነች ደግሞ ከፊቷና ከመዳፎቿ በስተቀር ሁሉንም የሰውነቷን ክፍሎች በሶላት ወቅት መሸፈን አለባት።
  • አንድ ሙስሊም ሶላት በሚሰግድበት ወቅት ለሶላት አስፈላጊ (የሶላቱ አካል) የሆኑትን ንግግሮችን ብቻ ይናገር፤ ኢማሙን (የሕብረት ሶላት የሚመራውን ሰው) በጥሞና ያዳምጥ፤ ሶላት ውስጥ ሆኖ ወደ ግራና ቀኝም አይዟዟር፣ ሶላት ውስጥ የሚባሉትንም ቃላት መሸምደድ ካልቻለ ሶላቱ እስኪያልቅ ድረስ ሱብሓነሏህ እና መሰል ዚክሮችን እያለ አላህን ያውሳ፤ ያወድሰውም፤ ይሁን እንጅ ሶላትን እና በውስጡ የሚባሉ ቃላቶችን ለመማር መቻኮል ይጠበቅበታል።

ራሴን ለሶላት አዘጋጃለሁ

ልሰግደው ያሰብኩትን ሶላት እነይታለሁ፤ በልቦናየ አስበዋለሁ።
ውዱእ ካደረግኩም በኋላ ወደ ቂብላ (መካ ወደሚገኘው ካዕባህ) አቅጣጫ እቅጣጫለሁ፤ ከቻልኩኝ ቆሜ እሰግዳለሁ።

በሁለተኛ ደረጃ፡ እጆቼን በትከሻዎቼ ትይዩ አንስቼ ወደ ሶላት ውስጥ ለመግባት በማሰብ “አላሁ አክበር” እላለሁ።

በሶስተኛ ደረጃ: ከነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) የተዘገበውን የመክፈቻ ዱዓ (ዱዓኡል ኢስቲፍታሕ) እላለሁ። ከመክፈቻ ዱዓዎች መካከል አንዱ የሚከተለው ነው፦
(ሱብሓነከ አልላሁመ ወቢሐምዲከ፤ ወተባረከ ኢስሙከ፤ ወተዓላ ጀዱከ፤ ወላኢላሃ ገይሩከ) ((ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን፤ ስምህ የተባረከ ነው፤ ልዕልናህም የተከበረ ነው፤ ካንተ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው የለም።))

የተረገመ ከሆነው ሰይጣን በአላህ ለመጠበቅ እንዲህ እላለሁ፦ (አዑዙ ቢላሂ  ሚነ-ሽሸይጧን አርረጂም) ((ትርጉሙም: ከተረገመው ሰይጣን በአላህ እጠበቃለሁ))

ሱረቱል ፋቲሓን (አልሓምዱን) በየረከዓው (የሶላት እያንዳንዱ ክፍል) እቀራለሁ። {ትርጉሙ: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (1) ትርጉሙ ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ የተገባው ነው (2) ትርጉሙ እጅግ በጣም አዛኝ አዛኝ እጅግ በጣም ሩኅሩህ (3) የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው፡ (4) አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን (5) ቀጥተኛውን መንገድ ምራን (6) ትርጉሙ የእነዚያ ፀጋህን የዋልክላቸውን ሰዎች መንገድ በነዚያ የተቆጣህባቸውን እና የተሳሳቱትንም አይደሉም። (7)} ከሱረቱል ፋቲሓ በኋላ በመጀመሪያው እና በሁለተኛው ረከዓ ብቻ ሌሎች (ከአልፋቲሃ ውጪ) ያሉ የቁርዓን አንቀጾችን አነባለሁ። ሌሎች የቁርኣን አንቀጾችን ማንበብ ግዴታ አይደለም ነገር ግን ማድረጉ ትልቅ ምንዳ ያስገኛል።

“አላሁ አክበር” ብዬ ከዚያም ጀርባዬ ቀጥ ብሎ በሚስተካከልበት ልክ በማጎንበስ፣ እጆቼ በጉልበቶቼ ላይ ጣቶቼን ከፈትፈት አድርጌ ሩኩዕ አደርጌ ሳለሁ “ሱብሓነ ረቢየ-አል-ዐዚም” እላለሁ። (ትርጉሙም: ታላቁ ጌታዬ ጥራት ተገባው)

“ሰሚዐ’ሏሁ ሊማን ሐሚደህ” እያልኩ ከሩኩዕ ቀና እላለሁ። (ትርጉሙም: አላህ የአመስጋኙን ምስጋና ሰማ) እላለሁ። እጆቼንም በትከሻዎቼ ትይዩ ከፍ እያደረግኩኝ እነሳና ቀጥ ብዬ ስቆም፡- “ረብበና ወለከል ሐምድ” እላለሁ። (ትርጉሙም: ጌታችን ሆይ! ምስጋና ላንተ ነው)

“አላሁ አክበር” እያልኩ በእጆቼ፣ በጉልበቴ፣ በእግሬ ጣቶች፣ በግንባሬና በአፍንጫዬ መስገጃየ ላይ ተደፍቸ ሱጁድ አደርጋለሁ። ከዚያም ሱጁድ ላይ (በግንባሬ ተደፍቼ) እያለሁም እንዲህ እላለሁ፡- “ሱብሐነ ረብቢየል-አዕላ” እላለሁ። (ትርጉሙም: ከሁሉ የበላይ የሆነው ጌታዬ ጥራት ተገባው)

“አላሁ አክበር” እያልኩ ከሱጁድ (ስግደት) ቀና ብየ ጀርባዬን ቀጥ አድርጌ በግራ እግሬ ውስጠኛው ክፍል ተቀምጬ የቀኝ እግሬን ተረከዝ ደግሞ ቀጥ አድርጌ እተክለዋለሁ። ከዚያም፡- “ረብቢ ኢግፊር ሊ” እላለሁ።(ትርጉሙም: ጌታዬ ሆይ! ኃጢአቴን ማረኝ)

“አላሁ አክበር”  እያልኩ እንደገና ልክ እንደ መጀመሪያው ሱጁድ አደርጋለሁ።

“አላሁ አክበር” እያልኩ ተስተካክየ ከሱጁድ እነሳለሁ፤ ከዚያም ይህንን በመጀመርያዋ ረከዓ ያደረግኩትን ስርአት ሁሉ በቀሪዎቹ የሶላት ክፍሎችም ላይ እፈጽመዋለሁ።

ከዙህር፣ ዐስር፣ መግሪብ እና ዒሻእ ሶላት ሁለተኛ ረከዓ በኋላ የመጀመሪያውን ተሸሁድ (አተሕያቱ) ለማለት እቀመጣለሁ። ይሀውም፦ “አት-ተሒያቱ ሊላሂ ወስ-ሶላዋቱ ወጥ-ጠይ-ዪባቱ፣ አስ-ሰላሙ ዐለይከ አይዩሀን-ነቢይዩ ወረሕመቱልላሂ ወበረካትሁ፤ አስሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲላሂ አስሷሊሒነ፣ አሽሀዱ አንላኢላሀ ኢልለልላህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ፡፡” “ትርጉሙም: ክብርና ልዕልና እንዲሁም ሶላቶችና መልካም ነገሮች ሁሉ ለአላህ ናቸው። አንቱ ነቢዩ ሆይ! የአላህ ሰላም፣ እዝነቱና በረከቱ በእርሶ ላይ ይስፈን፤ ሰላም በእኛና በአላህ ደጋግ ባሮችም ላይ ይስፈን፤ ከአላህ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ሙሐመድም የአላህ ባርያና መልዕክተኛው መሆናቸውንም እመሰክራለሁ፡፡” ከዚያም ለሦስተኛው ረከዓህ እቆማለሁ።


በእያንዳንዱ ሶላት የመጨረሻ ረከዓ ላይ የመጨረሻውን ተሸሁድ ለማለት እቀመጣለሁ። ይሀውም፦ “አትተሒያቱ ሊላሂ ወስሶላዋቱ ወጥጠይዪባቱ ፣ አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀን-ነቢይዩ ወረሕመቱልላሂ ወበረካትሁ ፤ አስሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲላሂ አስሷሊሒነ ፣ አሽሀዱ አንላኢላሀ ኢልለልላህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ፡፡ አልላሁምመ ሰልሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ሶልለይተ ዐላ ኢብራሂመ ወዐላ ኣሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፡፡ አልላሁምመ ባሪክ ዓላ ሙሐመዲን ወዐላ አሊ ሙሐመዲን ከማ ባረክተ ዐላ ኢብራሂመ ወዓላ አሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ።” “ትርጉሙም: ክብርና ልዕልና እንዲሁም ሶላቶችና መልካም ነገሮች ሁሉ ለአላህ ናቸው። አንቱ ነቢዩ ሆይ! የአላህ ሰላም፣ እዝነቱና በረከቱ በእርሶ ላይ ይስፈን፤ ሰላም በእኛና በአላህ ደጋግ ባሮችም ላይ ይስፈን። ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ሙሐመድም የአላህ አገልጋይና መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ፤ አላህ ሆይ! ውዳሴህን ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸው አውርድላቸው፤ አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና። አላህ ሆይ! ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው ረድዔትን እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸውም ረድዔትን አውርድላቸው። አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና።”

ያንን ሁሉ ካደረግኩ በኋላ ሶላቴን ለማጠናቀቅ በማሰብ ጭንቅላቴን ወደ ቀኝ እያዞርኩኝ “አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ” (ትርጉሙም: የአላህ ሰላምና እዝነት በናንተ ላይ ይሁን) ከዚያም ጭንቅላቴን ወደ ግራም እያዞርኩኝ “አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ” እላለሁ። ይህንን ባደረግኩ ጊዜ የሶላት ተግባሬን ፈጸምኩ ማለት ነው።

የሙስሊም ሴት ሒጃብ

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።} [አል አህዛብ ፡ 59]

አላህ ሙስሊም ሴት ላይ ሒጃብ መልበስ፣ “ዓውራ”ዋን ብሎም መላ የአካል ክፍሏን ለእርሷ ባዕድ ከሆኑ ወንዶች በሀገሯ (በአካባቢዋ) በተለመዱ ልብሶች እንድትሸፍን ግዴታ አድርጎባታል። ባሏ እና ከዝምድናዋ አንፃር ለጋብቻ የማይፈቀዱላት (መሕረሟ) ዘንድ ካልሆነ ሒጃቧን ማውለቅ አይፈቀድላትም። “መሕረም” ማለት፦ አንዲት ሙስሊም ሴት ከዝምድና አንፃር ማግባት ፍፁም የማይፈቀድላቸው ናቸው፤ እነርሱም፦ አባት ወደ ላይ ከፍ ቢልም፣ ልጅ ወደ ታች ዝቅ ቢልም፣ በሁለቱም ወላጆች በኩል ያሉ አጎቶችና አክስቶች፣ ወንድም፣ የወንድም ልጆች፣ የእህት ልጆች፣ (አብሯት ያደረ ከሆነ) የእናት ባል፣ የባል አባት ከፍ ቢልም፣ የባል ልጅ ዝቅ ቢልም፣ የልጅ ባል እንዲሁም በደም ዝምድና ክልክል የሆነ ሁሉ በጥቢም ይከለከላል።

ሴት ልጅ ሒጃቧን ስትለብስ መጠበቅ ያለባት መስፈርቶች፦

 

  • የመጀመሪያሙሉ የአካል ክፍልን የሚሸፍን መሆን አለበት።
  • ሁለተኛአንዲት ሴት ራሷን ለማስጌጥ ብላ የምትለብሰው ልብስ መሆን የለበትም።
  • ሦስተኛየውስጥ አካሏን (ገላዋን) የሚያሳይ መሆን የለበትም።
  • አራተኛሰፊና ለቀቅ ያለ እንጅ የተጣበቀ ሆኖ የሰውነት ቅርጿን የሚያሳይ መሆን የለበትም።
  • አምስተኛአምስተኛ፡ ሽቶ የተቀባ መሆን የለበትም።
  • ስድስተኛከወንዶች ልብስ ጋር የተመሳሰለ መሆን የለበትም።
  • ሰባተኛሙስሊም ያልሆኑ ሴቶች በአምልኳቸውም ሆነ በበዓላቶቻቸው
  •                        የሚለብሱት ልብስ ጋር የተመሳሰለ መሆን የለበትም።

 

ከሙእሚን (አማኝ) ባህሪያት መካከል

የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡- {ፍጹም ምእምናን እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ በነሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው።} [አል አንፋል፡ 2]

ከሙእሚን (አማኝ) ባህሪያት መካከል

  • በንግግሩ እውነተኛ ነው አይዋሽም።
  • ቃል ኪዳኑንም ይሞላል፤ ቃሉንም ይፈጽማል።
  • በክርክርም ጊዜ ድንበር አያልፍም።
  • አማና (አደራን) ይወጣል።
  • ለራሱ የሚወደውን ለሙስሊም ወንድሙም ይወዳል።
  • ቸር ነው።
  • ለሰዎችም መልካም (በጎ) ይውላል።
  • ዝምድናንም ይቀጥላል።
  • የአላህንም ቀደር (ቅድመ ውሳኔ) ወዶ ይቀበላል፤ በምቾት ጊዜ አላህን ያመሰግናል በችግር ጊዜ ደግሞ ይታገሳል።
  • ሐያእ (ሀፍረትን) የተላበሰ ነው።
  • ለፍጥረታት አዛኝ ነው።
  • ልቡ ከምቀኝነት የፀዳ፤ አካሉ ደግሞ በሌሎች ላይ ድንበር ከማለፍ ንፁህ ነው።
  • ለሰዎችም ይቅር ባይ ነው።
  • አራጣ አይበላም በእርሱም አይሠራም።
  • ዝሙትን አይፈጽምም።
  • አስካሪ መጠጥ አይጠጣም።
  • ለጎረቤቶቹም መልካምን ይውላል።
  • አይጨቁንም አያታልልም።
  • አይሰርቅም አይተናኮልም።
  • ወላጆቹ ሙስሊም ባይሆኑም እንኳን በጎ ይውልላቸዋል፤ በመልካም ነገርም ይታዘዛቸዋል።
  • ልጆቹን በመልካም አስተዳደግ ይንከባከባቸዋል፣ ሸሪዓዊ ግዴታቸውንም እንዲወጡ ያዛቸዋል፣ ከመጥፎ እና እርባነ ቢስ ከሆኑ ነገሮችም ይከለክላቸዋል።
  • ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች በሃይማኖታዊ ስርዓታቸውም ይሁን የእነርሱ መለያና መገለጫ በሆኑ ድርጊቶቻቸው እነርሱን አይመስልም።

ደስታዬ በእስልምና ሃይማኖቴ

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡- {ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።} [አን-ነሕል 97]

በሙስሊም ልብ ውስጥ ደስታን እና ምቾትን ከሚፈጥሩ ታላላቅ ነገሮች አንዱ የማንም ህያውም ይሁን ሙት ወይም ጣዖታት ጣልቃ ገብነት ሳያስፈልገው ከጌታው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት መፍጠሩ ነው። ከፍ ያለው አላህ በተከበረ ቁርኣኑ ላይ ሁል ጊዜ ለባሮቹ ቅርብ እንደሆነ፣ ዱዓቸውንም እንደሚሰማቸውና ምላሽም እንደሚሰጣቸው ተናግሯል። ጥራት ይገባውና የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡- {ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና።} [አልበቀራህ፡186]
ጥራት ይገባውና የላቀው አላህ እንድንለምነው (ዱዓእ እንድናደርግ) አዞናል፤ ይህንንም ጉዳይ (ዱዓእን) አንድ ሙስሊም ወደ ጌታው ከሚቃረብበት ታላላቅ ዒባዳዎች (አምልኮዎች) መካከል አንዱ እንዲሆን አድርጎታል። አላህ እንዲህ ብሏል፡- {ጌታችሁም አለ፤ ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና።} [ጋፊር፡60] መልካም የሆነ እውነተኛ ሙስሊም ዘወትር ጌታውን ከጃይ ነው። ሁልጊዜም አላህን መለመን እና በመልካም ስራም ወደ እርሱ መቃረብ ይጠበቅበታል።
አላህ በዚህ ከውን (ፍጥረተ ዓለም) ውስጥ ያስገኘን ለታላቅ ጥበብ እንጂ በከንቱ አልፈጠረንም፤ ይሀውም የተፈጠርንበት ጥበብ እርሱን ብቻ በብቸኝነት እንድናመልክና በእርሱ ላይ ምንንም እንዳናጋራ ነው። ማህበራዊም ሆነ ግላዊ የሕይወት ጉዳያችንን ስርዓት የሚያስተካክል የተሟላ መለኮታዊ ሃይማኖት ደንግጎልናል። በዚህም ፍትሃዊ የሆነ የሸሪዓ ህግ አምስቱን የህይወት አስፈላጊ መሰረቶችን ማለትም ሃይማኖታችን፣ ሕይወታችን፣ ክብራችን፣ አዕምሮአችን እና ንብረታችን ጠብቆልናል። በመሆኑም የሸሪዓን መመርያ በመከተል ክልከላዎቹንም (እርም የተደረጉትን) በመራቅ ህይወቱን የኖረ ሰው በርግጥም እነዚህን አስፈላጊ መሰረቶችን ተጠብቆለት አስደሳችና የተረጋጋ ህይወትን ይኖራል።
ሙስሊሙ ከጌታው ጋር ያለው ቁርኝት (ትስስር) እጅግ ጥልቅ በመሆኑ ለነፍሱ መረጋጋትና ዘና ማለትን ይፈጥራል፤ ደህንነት እና ደስታንም ይጎናፀፋል፤ አላህ ከእርሱ ጋ እንደሆነ እና እንክብካቤውና ጥበቃው ከእርሱ የማይለየው እንደሆነ እንዲሰማው ያደርጋል። አላህ እንዲህ ብሏል፡- {አላህ የእነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ነው፡፡ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል} [አል-በቀራህ: 257]፡፡
ይህ ታላቅ ግንኙነት ሙስሊሙን እጅግ በጣም አዛኝ የሆነውን አላህን በማምለክ የደስታ ስሜት እንዲሰማው እና እርሱን ለመገናኘት እንዲመኝ የሚያደርግ መንፈሳዊ ሁኔታ ነው። የእምነትን (የኢማን) ጥፍጣና ሲያጣጥም ልብን በደስታ ይሞላል።
ይህን የኢማን ጥፍጥና መልካም ሥራን በመስራትና ከመጥፎ ነገር በመራቅ ከቀመሰው በቀር ደስታውን ማንም ሊገለጽ አይችልም። ለዚህም ሲሉ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን እንዲህ ብለዋል፡-“አላህን ጌታው፣ እስልምናን እንደ ሃይማኖቱ፣ ሙሐመድን መልእክተኛ አድርጎ ወዶ የተቀበለ በርግጥ የእምነትን ጣእም ቀምሷል“።
አዎን! አንድ ሰው በፈጣሪው እጅ ውስጥ መሆኑን ከተረዳ፣ እጅግ ያማሩ መልካም ስሞቹንና ምሉዕ የሆኑ ባህሪያቱንም ካወቀ፣ ልክ እንደሚያየው አድርጎ ቢያመልከው፣ አምልኮውን በፍፁምነት ለአላህ ብቻ ካደረገ እና ከእርሱ ውጪ ያለን ሌላ አካል ካልፈለገ በቅርቢቱ ዓለም መልካምና ደስተኛ ሕይወት በመጨረሻይቱም ዓለም መልካም ፍጻሜ ይኖረዋል።
በዚህ ዓለም ላይ በአማኝ ላይ የሚያጋጥሙትን መከራዎች እንኳን ሳይቀር ቃጠሏቸው በየቂን (በአላህ ላይ ባለን ሙሉ እምነት) ፣ የአላህን ውሳኔ ወዶ በመቀበል ይበርዳሉ፤ መልካምም ሆነ መጥፎ ቅድመ ውሳኔዎቹን ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ወዶ በመቀበልና እርካታውን በመግለፅ ያመሰግናል።
አንድ ሙስሊም ደስታውና እርጋታው እንዲጨምረለትና እንዲጎለብትለት ሊያደርግ ከሚገባቸው ነገሮች መካከል አላህን ደጋግሞ በብዛት ማውሳት እና የተከበረውን ቁርኣን ማንበብ ይገኙበታል፤ ልክ አላህ እንዳለው፦: {(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ} [አርረዕድ፡28] እናም አንድ ሙስሊም አላህን ማስታወስና ማውሳቱ እንዲሁም ቁርኣንን ማንበቡ በጨመረ ቁጥር ከፍ ካለው አምላክ አላህ ጋ ያለው ቁርኝት እየጨመረ፣ ነፍሱ እየፀዳች እና እምነቱም ጠንካራ እየሆነ ይሄዳል።
እንደዚሁም ሙስሊሙ ኃያሉን አሏህ በዕውቀትና በማስረጃ ላይ ሆኖ እንዲያመልክ ሃይማኖቱን ከትክክለኛ ምንጮች ለመማር ከፍተኛ ቁርጠኝነትና ጥረት ሊኖረው ይገባል። ነብዩ አላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን እንዲህ ብለዋል፡- “ዕውቀትን መፈለግ በሁሉም ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።”
( የእያንዳንዱ ኢስላማዊ ድንጋጌዎችን) ጥበብ አወቀውም አላወቀም ለፈጠረው አምላክና ከፍ ላለው አላህ ትእዛዛት መገዛት እና ታዛዥ መሆን ይገባዋል። {አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ።} [አል አሕዛብ፡36]

ምስጋና ለአላህ ይገባው፤ የዓለማት ጌታ ለሆነው፤ የአላህ እዝነትና ሰላምም በነቢያችን ሙሐመድ ላይ እና በቤተሰቡ እንዲሁም በባልደረቦቹ ላይ ይውረድ።